የቢዝነስ አቅጣጫዎች

የወደፊት መጠባበቂያ መዋጮ, የትምህርት መዋጮ, የጡረታ መዋጮ, ማዕከላዊ የጉዳት ክፍያ መዋጮ, የጋራ መዋጮ፤ ኢቲኤንስ, የስራ ማህደር ማስተዳደር፣ ምርምር እንዲሁም የድለላ አገልግሎት፡፡ በ 1956ዓ.ም. ተመሰረተ፡፡

የድርጅቱ አጭር ገፅታ

ፕሳጎት, በአፓክስ ሸሪኮች የሚመራ ሲሆን, የእስራኤል ትልቁ የኢንቨስትመንት ቤት ነዉ፡፡

በ1956ዓ.ም. ባንክ ሌይሚ ኦፌክ ሲኪሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንትስን አቋቋመ፤ እንዲሁም በ1982ዓ.ም ፕሳጎት ሙቱኣል ፈንድስን መሰረተ፡፡ በ1996ዓ.ም. ሁለቱ ድርጅቶች ወደ አንድ ተጣምረዉ ፕሳጎት ኢንቨስትመንት ሃዉስን አቋቋሙ፤ ይህም ፕሳጎትን በእስራኤል የካፒታል ገበያ ዉስጥ አንጋፋዉ እና በሙያዉ የረዥም አመት ልምድ ያለዉ ድርጅት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ የፕሳጎት ሰራተኞች ባለሙያዎች፣ በሚገባ የሰለጠኑ፣ ለስራዉ የተሰጡ እና ልምድ ያካበቱ እንዲሁም የካፒታል ገበያዉን መዋዠቆች ያሳለፉ ናቸዉ፡፡ ፕሳጎት ለማህበረሰቡ የረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንት አማራጮችን አቅርቧል፤ እነርሱም የወደፊት መጠባበቂያ መዋጮ፣ የትምህርት መዋጮ፣ ማዕከላዊ የጉዳት ክፍያ መዋጮ እና የጡረታ መዋጮ እንዲሁም የአጭር ጊዜ ተቀማጭ ሂሳቦች ለምሳሌ፡ የእስራኤል እና የዉጪ ኢንቨስትመንት አስተዳደር፣የጋራ መዋጮ, ኢትኤንስ, የድለላ እና የምርምር አገልግሎቶች፡፡ ፕሳጎት ከመላዉ እስራኤል ዉስጥ በጣም ትልቁ፣ ከፍተኛ-ጥራት ያለዉ ምርምር እና ዋጋ ያለዉ ሰራተኛ ያለዉ ድርጅት ነዉ፡፡ የኢኮኖሚዉ ግንባር ቀደም ድርጅቶች፣ የህዝብ ኢንስቲቲዉቶች፣ የኢንስቲቲዉት አካላት፣ የዉጪ ኢንቨስተሮች፣ እና ግለሰቦች ሁሉ ሀብታቸዉን ለማስተዳደር ፕሳጎትን ይመርጣሉ፡፡

የኢኮኖሚ ስኬል

ባለፈዉ አስር አመት ዉስጥ የተደረገዉ የቁጥጥር ህጎች መሻሻል እና ለዉጥ በእስራኤል የካፒታል ገበያ ላይ የጠለቀ የመዋቅር መሻሻል አምጥቷል፡፡ ፕሮፌሽናል የሆነ የገንዘብ ንብረት አስተዳደር ዉስብስብ የስራ ሂደት፣ ቁጥጥር እና አስተዳደራዊ መንገዶችን ይፈልጋል፡፡ የእኛ ኢንቨስትመንት ስብስብ ከደረጃ አስፈላጊ ጥቅም በማስገኘቱ ደስተኛ ሲሆን፤ ከኢንቨስትመንት ሂደት እና ግልጋሎቶች ጋር ተያይዞ ለአሰራር፣ የስራ ሂደት፣ ክትትል እና ቁጥጥር ጥራት በሚገባ ይሰራል፡፡

ቁጥጥር እና ማሟያ

የእኛ ኢንቨስትመንት ቡድን እንቅስቃሴዎች በተከታታይ እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በዉስጥ እና በዉጪ ወኪሎች ይገመገማል፡፡ ዉስጣዊ ክትትል የሚደረገዉ በቁጥጥር እና ሟሟያ ክፍል ሲሆን ይህ ክፍል ከሌሎች ነገሮች በተለየ በፕሳጎት ግሩፐ የተወረሰዉን የዉስጣዊ ማሟያ ፕሮግራምን ሙሉ እና ተጨባጭ ተፈፃሚነት በኃላፊነት ይሰራል፡፡ በተጨማሪም ዉስጣዊ የክትትል ደረጃዎች ሲኖሩ በተለያዩ ስራ ክፍሎች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እነሱም ዉስጣዊ ኦዲት፣ የአሰጋ ጥናት፣ እና ቁጥጥር ክፍሎች ናቸዉ፡፡ ዉጫዊ ቁጥጥር የሚካደዉ እንደ እስራኤል ሲኪዉሪቲስ፣ ዘቲኤኤስኢ፣ የእስራኤል መኒ ላዉንደሪንግ አዉቶሪቲ፣ እና ፋይናንስ ሚኒስቴር በመሳሰሉ የቁጥጥር ድርጅቶች ነዉ፡፡ እንዲሁም በዉጫዊ አማካሪዎች በመጠቀም ድርጅቱ ኦዲት እና ግምገማ ያደርጋል፡፡

የረዥም ጊዜ ተቀማጭ

የፕሮቪደንት መዋጮ፣ የትምህርት መዋጮ፣ እና ማእከላዊ የጉዳት ክፍያ ገንዘብ –  ፕሳጎት በረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንት ላይ ልምድ ያካበተ ሲሆን ምርጥ አፈፃፀም እና ከፍተኛ ምስጋና ያተረፈ ነዉ፤ የሚከተሉትን ግልጋሎቶች ይሰጣል፣ የፕሮቪደንት/መጠባበቂያ መዋጮ፣ የትምህር መዋጮ እና የማእከላዊ አደጋ ክፍያ መዋጮ፡፡ ከሌሎች በተለየ በመላዉ እስራኤል ትልቁ የሆነዉን የፕሮቪደንት መዋጮ የሆነዉን ጋዲሽን ያስተዳድራል፡፡

አዲስ የጡረታ መዋጮ – በጥር 2004 ዓ.ም. ፕሳጎት የድንበኞቹን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የኢንሹራንስ እና ኢንቨስትመንት አማራጮችን ያካተተ አዲስ የጡረታ መዋጮ አገልግሎት ጀምሯል፡፡ ፕሳጎት በትላልቅ የጡረታ መዋጮዎች መካከል ፍክክር መፍጠር እንደሚቻል እና ይህም በመላዉ እስራኤል የጡረታ መዋጮ ገበያ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያምናል፡፡

ኢንሹራንስ – በጥቅምት 2006 ዓ.ም. ፕሳጎት ኢንሹራንስ ድርጅት የሺርቢት ኢንሹራንስ ድርጅትን የህይወት ኢንሹራንስ የራሱ ንብረት አድርጓል፡፡ ይህ አዲስ ንብረት ከላዉ የቤቱ ኢንቨስትመንት ደረጃዎች ጋር በመጣመር ፕሳጎትን ለደንበኞቹ አስተማማኝ፣ የተጠበቀ፣ እና የፀና አግልግሎቶችን እንዲሰጥ አስችሎታል፡፡ 

 የአጭር ጊዜ ተቀማጭ

የጋራ መዋጮ–  ፕሳጎት የጋራ መዋጮ በእስራኤል ከሚገኙት ድርጅቶች ግንባር ቀደም ሲሆን አፈፃፁም ከጊዜ ወደ ጊዜ አጥጋቢ ሆኗል፡፡ ለተለያዩ ኢንቨስተሮች ምቹ የሆኑ ከ170 በላይ የጋራ መዋጮዎችን በተለያዩ መስመሮች ላይ ያንቀሳቅሳል፡፡ 

ኢቲኤንስ/የገበያ ልዉዉጥ -  የፕሳጎት ኢትኤንስ በእስራኤል እና በዉጪ ሀገር ቋሚ ንብረትን ለምሳሌ እንደ መለኪያዎች፣ ሸቀጦች፣ የገንዘብ ምንዛሬ የሚከታተሉ

 ከ 215 በላይ ኢቲኢንስን አቅርቧል፡፡ ድርጅቱ የሰለጠኑ፣ ፕሮፌሽናል የደላሎች ቡድንን ይዞ ዘመናዊ የመገበያያ ክፍልን ያንቀሳቅሳል፡፡

የማህደር አስተዳደር በእስራኤል እና በዉጪ ሀገራት

ፕላጎት ሰርቲፍስ ሲኪዉሪቲስ ለድርጅቶች፣ ኢንስቲቲዉቶች፣ የግል ኢንቨስተሮች ከኢንቨስትመንት አማራጮች ጋር ይዞ ለደንበኞቹ የኢንቨስትመንት ማህደርን የሚያስተዳድር ድርጅት ነዉ፡፡

የድለላ እና የምርምር አገልግሎቶች

የፕላጎት ድለላ ክፍል የኢንቨስትመንት እና የግል ኢንስቲቲዉቶች ከአለምአቀፍ ሲኪዉሪቲስ ፕሮፌሽናል ድለላ አገልግሎቶች እንዲሁም ከፕላጎት አገልግሎት እና ግዙፍ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች በአለማችን ላይ አሉ ከሚባሉ ቀዳሚ፣ ዘመናዊና የላቀ እንዲሁም የመጨረሻ ቴክኖሎጂ፣ ግንኙነት፣ ዳታ መዋቅር ያካተተ የግብይት መድረክ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ትልቅ እና ከፍተኛ ጥራት ያለዉ የምርምር ክፍል

ፕላጎት የደንበኞቹን ንብረት በላቀ እና ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለማስተዳደር ወሳኝ እና ቀጣይነት ያለዉ ምርምር አስፈላጊ እንደሆነ ያምናል፡፡ በፕላጎት የሚገኘዉ የኢንቨስትመንት እና የምርምር ክፈል በዉስጡ 6 ንኡስ ክፈሎች ያካተተ ሲሆን ፤ በዉስጡም ከ 80 በላይ አጥኚዎች ኢንቨስትመንት ስራ አስጂያጅ፣ እና በስስራኤል ሲኪሪቲስ በላስልጣን ፈቃድ ያገኙትን ገበያተኞች አኳቷል፡፡ እነርሱም ሌትተቀን ከፍተኛ ደረጃ ጥናት እየሰሩ  ፕላጎት በላቁ የገንዘብ ድርጅቶች ተርታ እንዲሰለፍ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም ፕላጎት በእስራኤል እና በሌላዉ አለም የሚገኙትን መሪ የኢንስቲቲዎች እውቀት በቋሚነት ይጠቀማል፡፡

የኢንስቲቲዉት ጣልቃገብነት

ፕላጎት ራሱን የቻለ የኢንቨስትመንት ጣልቃ ገብነት ክፍል በማቋቋም የመጀመሪያዉ የኢንቨስትመንት ድርጅት ነዉ፡፡ ይህ ክፍል በኢንቨስትመነት የጊዜ ገደብ ዉስጥ የደንበኛዉን መብቶች በሚገባ መከበሩን እንደ ግብ ወስዶ ይንቀሳቀሳል፡፡ በ2005ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ፕላጎት ለደንበኞቹ ተአማኒነት እና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጉ የኢንስቲቲዉቱ ጣልቃገብነት መርሆችን አዉጥቷል፡፡ እነዚህ መርሆች ፕላጎት ኢንስቲቲዉሽናል ቻርተር በመባል በይፋ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቻርተር ለግልፅ፣ ተጠያቂነት እና ሊገመት የሚችል የስራ ስነምግባር የሚተመን ሲሆን የታተመ እና በድርጅቱ ድረ-ገፅ የሚገኝ ነዉ፡፡

 

የማህበር ህብረተሰባዊ ኃላፊነት

የማህበረሰብ ህብረተሰባዊ ሃላፊነት ዋነኛ የሆነዉን የእኛ ኢንቨስትመንት ድርጅት የስራ እቅድ እና የቢዝነስ ስትራቴጂ ይገልፃል፡፡ ፕላጎት ራሱን ለህብረተሰቡ እና ማህበረሰቡ የቆመ አድርጎ የሚያስብ ሲሆን በማህበረሰብ ተሳትፎ እና በሰራተኞች የፈቃደኝነት ስራ የበለጠ ከማህበረሰቡ ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡

የማላ ሽልማት – ፕላጎት የፕላቲኒየም ተሸላሚ ሆኗል፤ ይህም በ2006ዓ.ም. በተካሄደዉ የመላ ሽልማት ላይ በ ሲኤስአር ትልቁ ነዉ፡፡ ይህንን የክብር ሽልማት ስናሸንፍ አሁነወ ለተከታታይ 6ኛ ጊዜ ነዉ፡፡

 

ፕላጎት የእዉቀት ማዕከል ለፋይናንስ ትምህርት

በጣም ጠቃሚዉ የፋይናንስ መሳሪያ እዉቀት ነዉ፡፡ ፕላጎት የኢንቨስትመንት መድረክ፤ ከእስራኤል ትልቁ የማህበረሰብ መዋጮ አስተዳደር ሲሆን፤ የፕላጎትን የፋይናንስ እዉቀት ማእከል ወደ ሚሊዮን ደንበኞች እና ለእስራኤል ማህበረሰብ ክፍት አድርጓል፡፡ ይህ ማዕከል ዘመናዊ የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ መሳሪያዎችን ያቀረበ ሲሆን ሰዎች ገንዘባቸዉን ማስተዳደር እንዲችሉ ለመርዳት እና የተለመዱ የፋይናንስ ስህተቶችን ለማስወገድ ያለመ ነዉ፡፡

አድራሻ: አሃድ ሃም 14, ቴል አቪቭ, 6514211

ስልክ.: 03-7968805               ፋክስ: 03-7968889

 

 ኢሜይል: pniyot@psagot.co.il ድረ-ገፅ: www.psagot.co.il

 

የጋራ መዋጮ አስተዳደር – ፕላጎት የጋራ መዋጮ ሊሚትድ

^የላይኛዉ የተወሰነ ትርፍን ለማግኘት ቃል አይገባም፡፡

ቀድሞ ከላይ የተገለፀዉ ኢንቨስትመንት ማሻሻጥ/ምክር እና/ወይም የጡረታ ምክር/ማሻሻጥ ወይም/እና የምክር/ማሻሻጪያ አማራጭ ወይም/እና የታክስ ምክር አያካትትም፤ ይህ እንደየ ደንበኛዉ ፍላጎት መሰረት ያደረገ እና የጋራ መዋጮ እና/ወይም ኢትኤንስ ወይም/እና ሲኪዉሪቲስ ለመሸጥ የቀረበ አይደለም፡፡ የመዋጮ ግዢ እና/ወይም ኢትኤን አግባብነት በላዉ ዉሳኔና አስቸኳይ ሪፖርት ብቻ መፈፀም አለበት፡፡ የላይኛዉ የተወሰኑ ትርፍን ለማግኘት ቃል አይገባም፡፡ ፕላጎት ሲኪዉሪቲስ ሊሚትድ- የማህደር አስተዳደር እና አክስዮን ልዉዉጥ አባል እና ፕላጎት ኢንቨስትመንት ቤት ሊሚትድ - ኢንቨስትመንት ሻጭ /ለድርጅቶች/ ለኢንቨስትመንት ማሻሻጥ ላይ ይሰራል /በኢንቨስትመንት ማማከር ላይ አይሰራም/ እና የፕላጎት ግሩፕ አባል ነዉ፡፡ ድርጅቶቹ እርስ በእርስ የሚደጋገፍ/አብረዉ የሚሰሩ/ ሲሆን የጋራ መዋጮ በፕላጎት የፕሮቪደንት መዋጮ እና ጡረታ ሊሚትድ ይተዳደራል፡፡ ኢንቨስትመንታቸዉ በፕላጎት ሲኪዉሪቲስ የሚተዳደሩ ፕሮቪደንት መዋጮዎች በፕላጎት ኤክስቼንጅ ትሬድ ኖትስ ሊሚትድ ይተዳደራሉ፡፡ በፕላጎት ባይንዲንግ ሰርተፊኬሽን የዉጪ ምንዛሬ  ሊሚትድ፤ በፕላጎት ኤክስቼንጅ ትሬድድ ኖትስ ኢንዲክስስ ሊሚትድ፤ በፕላጎት ኢንዴክስስ ፕሮዳክሽን ሊሚትድ፤ ፕላጎት ፕሮዳክሽን ሊሚትድ፤ ፕላጎት ኳርትርለ ሊሚትድ፤ ፕላጎት ከረንሲስ ሊሚትድ እና ፕላጎት ኔጎሽብል ዶላር ኢባሉኤሽን ሊሚትድ በሚባሉ ንዑስ ደርጅቶች ይተዳደራሉ፡፡ ፕላጎት ፕሮቪደንት መዋጮ እና ጡረታ ሊሚትድ በጡረታ ማሻሻጥ (የጡረታ ማማከርን አያካትትም) ከጡረታ ፕሮቪደንት ኢንደርኢትስ አስተዳደር ጋር አብሮ ይሰራል፡፡

 

​​​ 

  

​​